About-ስለ እኛ

ቃለ ዐዋዲ አገልግሎት

ቃለ ዐዋዲ በተለያዩ ጉባኤዎችና በቴሌብዥን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለሰዎች ሁሉ የሚያበስር አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ መጠን ወንጌሉን ለሰዎቹ ሁሉ በያሉበት ለማድረስና የእግዚአብሔርን የምህረትና የፍቅር ወንጌል ለማብሰር እናገለግላለን።
መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ መስቀል ላይ ለኛ ለሰው ልጆች የገለጠውን ነፍሱን እስከመስጠት የደረሰ ፍቅር ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙትና ልባቸው በእግዚአብሔር ፍቅር እንዲማረክ በዚህ በቃለ ዐዋዲ ያለን ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ከርሱ በተቀበልነው ጸጋ መጠን እያገለገልን
የቃለ ዐዋዲ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ ሁሉ በሚያሰራጨው የቴሌብዥን አገልግሎት ድንበር ሳይገድበው ብዙዎችን እየጠቀመ ሲሆን አሁንም የበለጠ ለብዙዎች እንዲደርስ ከኛ ጋር አብረው እንዲቆሙ በእግዚአብሔር ፍቅር እንጋብዝዎታለን።